"ኑ ቸርነትን እናድርግ!"
- Raised
- $7,975
- Goal
- $50,000
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካሏት ሀብት መካከል ዋናዎቹ ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ ብዙ ቅዱሳን አባቶች እና ሊቃውንትን ያፈራችበት ተቋማቶቿ ናቸው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት ወስጣዊ እና ውጫዊ ፈተናዎች ሲገጥማት ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችም አብረው ተፈትነዋል፣ ተሰደዋል፣ ተፈተዋል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ቃል የሚነገረባቸው በመሆኗቸው ዘርፈ ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁመው ዛሬ ላይ ደርሰዋል፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን በተከሰተው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት በተለይ በአማራ ክልል አኅጉረ ስብከት የሚገኙ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ለተለያዩ ተግዳሮቶች ተጋልጠዋል፡፡ ገዳማት ዘወትር ከሚጎበኟቸው ምዕመናን ጋር ተለያተዋል፣ ያፈሩት ንብረታቸው ተዘርፎባቸዋል፤ በዚህም ለቀለብ ችግር ተዳርገዋል፡፡ በተመሳሳይ የአብነት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ተገለዋል፣ ተሰደዋል፣ ንብረታቸው ተዘርፏል ጉባኤ ቤቶችም ተበትነዋል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የእምነቱ ተከታዮች ምዕመናንን በማስተባበር የተለያዩ አስቸኳይ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡
ምንም እንኳ ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ ባይቆምም እንደ ቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገለግሎት ማስተባበሪያ አልፎ አልፎ አንጻራዊ ሰላም በሚታይባቸው ቦታዎች ላይ የችግር ተጋላጭ የነበሩትን ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ምእመናንን በማስተባበር በገንዘብ ለመደገፍ በመታሰቡ ይህ የድጋፍ ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፡፡ ይህም ድጋፍ በ40 የአብነት ት/ቤቶች ለሚገኙ መምህራን እና ደቀመዛሙርት እንዲሁም በ27 ገዳማት ለሚገኙ መናንያን የቀለብ ድጋፍ የሚውል ይሆናል።
1. የመርሐ ግብሩ ዓላማ፡-
1.1. ዋና ዓላማ፡-በአማራ ክልል ያሉ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች አሁን ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ገዳማቸዉ እንዳይፈታ እና ጉባኤያቸዉን እንዳያጥፉ በመደገፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማስቀጠል ነው፤
1.1. ዝርዝር ዓላማ፡-
v በረሃብ ምክንያት አብነት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ማድረግ፤
v በቀለብ ችግር መነኮሳት ገዳማቸዉን ጥለዉ እንዳይሰደዱ ማገዝ፤
v በወቅታዊ ችግሩ ምክንያት የወደሙባቸዉን ንብረቶች በጊዜያዊነት እንዲተኩ ማስቻል፤
v ገዳማውያኑ ጸሎታቸውን ደቀ መዛሙርት ትምህርታቸዉን ተረጋግተዉ እንዲማሩ ማስቻል ነው፡፡
2. የፕሮጀክቱ ቆይታ
ፕሮጀክቱ የገዳማቱንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ጊዜያዊ ችግር ለመፍታት የታሰበ እንደመሆኑ ድጋፉ ለአንድ ዓመት ከግንቦት 2016 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 2016 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።
ስለሚያደርጉት ድጋፍ ሁሉ በመምህራኑ፣ በደቀመዛሙርቱ እና በገዳማዉያኑ ስም እግዚአብሔር የነፍስ ዋጋ ያድርግልን!